በእያንዳንዱ ትዕዛዝ ብቃት።

ብዙ ደንበኛ ቢኖርዎትም በወሩ መጨረሻ “ትርፉ የት ገባ?” ብለው ይጠይቃሉ። ማጀት ከግዢ እስከ ሳህን እያንዳንዱን እቃ ይከታተላል። እውነተኛ ወጪዎን ያውቃሉ፣ ብክነትን ይቀንሳሉ፣ ዋጋን በመረጃ ይወስናሉ።

በነጻ ይሞክሩ

የማዋቀር እገዛ ይካተታል · ካርድ አያስፈልግም

ይህ ያጋጥምዎታል?

ኩሽናው ስራ በዝቶበታል። ጠረጴዛዎች ሞልተዋል። ትርፍ ግን ትንሽ ነው።

ብዙ ምግብ ቤቶች ደንበኛ ቢኖራቸውም ወጪ ስለማይቆጣጠሩ ትርፍ እያጡ ነው።

  • በግምት የሚደረግ ግዢ

    የጥሬ እቃ ክምችት በአግባቡ አይታወቅም፤ ምን ተጠቀምን፣ ምን ጠፋ፣ ምን ቀረ የሚል ግልጽ መረጃ የለም።

  • የተደበቀ ብክነት

    መበላሸት፣ ከመጠን በላይ መጠቀም እና የኩሽና ኪሳራ አይመዘገብም፤ ስለዚህ አይስተካከልም።

  • በግምት የሚወሰን ዋጋ

    የምግብ ዋጋ ከእውነተኛ ወጪ ይልቅ በጎረቤት ምግብ ቤት ዋጋ ይኮረጃል።

  • የማይመጣጠን ምግብ

    አንድ አይነት ምግብ እንደ አብሳዩ ጣዕሙም ወጪውም ይለያያል።

አንድ ስርዓት፣ ከግዢ እስከ ሳህን

ትርፋማ ኩሽና ለማስተዳደር የሚያስፈልግዎ ሁሉ

  • 01

    የሜኑ እና ሬሲፒ ገንቢ

    እያንዳንዱን ምግብ በትክክለኛ የአስቤዛ መጠን ይገንቡ። የአንድ ሳህን ወጪ ከወቅታዊ የአስቤዛ ዋጋ በራሱ ይሰላል።

  • 02

    የክምችት ቁጥጥር

    የእያንዳንዱ አስቤዛ እንቅስቃሴ በቀጥታ፣ አስቤዛ ከማለቁ በፊት ማስጠንቀቂያ፣ እና በቀላሉ እንደገና ማዘዝ።

  • 03

    የብክነት መቆጣጠሪያ

    ብክነትን በአስቤዛ፣ በምድብ፣ በፈረቃ እና በምክንያት ይመዝግቡ። ገንዘብ የት እንደሚፈስ በግልጽ ይመልከቱ።

  • 04

    ወጪ እና ዋጋ አወጣጥ

    የሚፈልጉትን የትርፍ ህዳግ ያስቀምጡ፤ የሚመከር የሽያጭ ዋጋ ያግኙ።

  • 05

    የንግድ ትንተና

    ዕለታዊ ሽያጭ፣ የወጪ አዝማሚያ፣ በብዛት እና በትንሹ የሚሸጡ፤ በቁጥር ላይ በመመስረት ውሳኔ ይስጡ።

  • 06

    የቡድን አሰራር

    ለባለቤት፣ ለኩሽና፣ ለካሸር እና ለአስተናጋጅ ግልጽ ሚና። በስራ ሰዓት ውዥንብር ይቀንሳል።

ለመላው ቡድን የተሰራ

ለእያንዳንዱ ሚና የሚያስፈልገው ስክሪን

ሙሉ ንግድዎን በአንድ እይታ

  • ሽያጭ፣ የምግብ ወጪ እና ትርፍ በአንድ ዳሽቦርድ
  • በብዛት እና በትንሹ የሚሸጡ ምግቦች
  • ሰራተኞች፣ ቦታ ማስያዝ፣ ግምገማዎች እና ደንበኞች በአንድ ቦታ
እንዴት ይሰራል

በሶስት ቀላል ደረጃዎች ይጀምሩ

  1. 1

    ምግብ ቤትዎን ይመዝግቡ

    መለያ ይክፈቱ፤ ቅርንጫፎችን፣ ጠረጴዛዎችን እና የሰራተኛ ሚናዎችን ያክሉ።

  2. 2

    እቃዎችን እና ሬሲፒዎችን ያስገቡ

    ክምችትዎን ያስገቡ፣ ሬሲፒ ይገንቡ፤ ማጀት የሳህን ወጪን በራስ ሰር ያሰላል።

  3. 3

    ይስሩ፣ ትርፍዎን ይመልከቱ

    ትዕዛዝ ይቀበሉ፣ ያብስሉ፣ ሂሳብ ይዝጉ፤ ክምችት፣ ብክነት እና ትርፍ በቀጥታ ይታደሳሉ።

መረጃ ሲጠራ ውሳኔ ይፈጥናል።

  • ብክነት ይቀንሳል
  • ወጪ ይታወቃል
  • ዋጋ በመረጃ ይወሰናል
  • ትርፍ ይጨምራል
ዋጋ

አንዴ ይክፈሉ። ስርዓቱ የእርስዎ ነው።

ማጀት በራስዎ ሰርቨር ላይ ይጫናል፤ መረጃዎ ከእርስዎ ጋር ይቆያል። እያንዳንዱ ግዢ የአንድ ዓመት ነጻ ድጋፍ ያካትታል፤ ልዩ ተግባራትን እና የስራ ሂደቶችን በስምምነት እንገነባለን። በብር የተመሰረተ ዋጋ ለማግኘት ያግኙን።

በእያንዳንዱ ግዢ የተካተተ

  • በራስዎ ሰርቨር

    በራስዎ ሰርቨር ላይ ይጫናል። መረጃዎ በእርስዎ ቁጥጥር ስር ነው።

  • የ1 ዓመት ነጻ ድጋፍ

    ከግዢ በኋላ ለአንድ ዓመት ነጻ ድጋፍ፣ ከማዋቀር እና ከሰራተኛ ስልጠና ጋር።

  • ልዩ ተግባራት

    ለምግብ ቤትዎ አሰራር የሚስማሙ ተግባራት እና የስራ ሂደቶች በስምምነት።

ዋጋ ይጠይቁ

ስለ ምግብ ቤትዎ ይንገሩን፤ ለእርስዎ የሚስማማ ዋጋ እናዘጋጃለን። በሚመችዎ መንገድ ያግኙን።

ጥያቄዎች

ባለቤቶች የሚጠይቁን ተደጋጋሚ ጥያቄዎች

ማጀት በምን መሳሪያዎች ላይ ይሰራል?

በላፕቶፕ እና ታብሌት ብራውዘር፣ እንዲሁም በአንድሮይድ እና iOS ስልኮች ላይ ይሰራል።

ፈጣን ኢንተርኔት ያስፈልገኛል?

መደበኛ የሞባይል ዳታ ወይም Wi-Fi በቂ ነው። መረጃ በሁሉም መሳሪያዎች ላይ በቀጥታ ይመሳሰላል።

የትኞቹ የክፍያ መንገዶች ይደገፋሉ?

ጥሬ ገንዘብ እና እንደ ቴሌብር፣ ቻፓ፣ ንግድ ባንክ እና አቢሲኒያ ባንክ ያሉ የሀገር ውስጥ ክፍያዎች ከቅንብሮች ሊዋቀሩ ይችላሉ።

መረጃዬ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?

ማጀት በራስዎ ሰርቨር ላይ ስለሚጫን መረጃዎ በእርስዎ ቁጥጥር ስር ነው። ሰራተኞች ለሚናቸው የሚያስፈልገውን ብቻ ያያሉ።

ለማዋቀር ታግዙናላችሁ?

አዎ። ሜኑዎን፣ እቃዎችዎን እና ሬሲፒዎችዎን እንዲያስገቡ እና ሰራተኞችዎን እንዲያሰለጥኑ እናግዛለን።

በአማርኛ ይገኛል?

አዎ፣ ይህ ድረ-ገጽ እና የማዋቀር ድጋፋችን በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ይገኛል።

ከዕለታዊ ውዥንብር ወደ ዕለታዊ ቁጥጥር።

እያንዳንዱን ትዕዛዝ በትክክል፣ በፍጥነት እና በትርፍ ያስተዳድሩ።

በነጻ ይሞክሩ

ነጻ ማሳያ ይጠይቁ

ስለ ምግብ ቤትዎ ይንገሩን፤ ማሳያ ለማዘጋጀት እንደውልልዎታለን።